በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ

ግንቦት 29/2014 (ዋልታ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።

ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ በአንድ ግለሰብ ቤት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርተር ተተኳሽ (ቅንቡላ) ተከዝኖ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤትን ዋቢ አድርጎ አሚኮ ዘግቧል፡፡

የተገኘው የሞርተር ተተኳሽ አሸባሪው ሕወሓት ቡድን ከአካባቢው ሸሽቶ ሲሄድ ጥሎት የሄደው ሊሆን እንደሚችልም የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያስታወቀው።

ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብም በሕግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተጠቁሟል።