በጎንደር የሰሜን እዝ ጥቃትን የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ጥቅምት 24 /2014 (ዋልታ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪው ሕወሓት ጥቅምት 24 ሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ በማሰብ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት አካሄዱ።
ነዋሪዎቹ አሸባሪው ሕወሓት ሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ አንደኛ ዓመትን ሲያስቡ አገራዊ ሁኔታውን ግምት ውስጥ በማስገባት ወራሪውን ቡድን በመፋለም ላይ ለሚገኝ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ በመቁረጥ እንደሆነም ገልፀዋል።