በጠ/ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የተመራ ልዑክ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ተወያየ

ሐምሌ 26/2014 (ዋልታ) በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ ልዑክ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ውይይት አድርጓል።

ልዑኩ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች፣ ወንጀልን በጋራ መከላከል፣ የመረጃ ልውውጥን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከሩን አምባሳደር ሬድዋን በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።