በጣሊያንና ግሪክ ለተፈናቃዮች ከ120 ሺሕ ዩሮ በላይ ድጋፍ ተደረገ

ታኅሣሥ 18/2014 (ዋልታ) በጣሊያን እና ግሪክ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአሻባሪው ሕወሓት ወራሪ ቡድን ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል 120 ሺሕ 783 ዩሮ ድጋፍ ማስረከባቸውን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
በሽብር ቡድኑ ወረራ ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ እና የወደሙ የኅብረተሰብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ቀጥለዋል፡፡
በተያያዘም ዲያስፖራው ወደ አገር ቤት እንዲገባ የተደረገለትን ጥሪ በመቀበል ወደ አገር ቤት መግባት ጀምሯል።
የዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባላቱ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚሆን የዓይነት ድጋፍ በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው ተብሏል፡