በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን በበይነ መረብ እያገዙ ለሚገኙ ዲያስፖራዎች መንግሥት ምስጋና አቀረበ

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ታኅሣሥ 25/2014 (ዋልታ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኢትዮጵያ ተጣርታ አልቀርም ብለው ወደ ሀገራቸው ለመጡ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

“ኢትዮጵያ ተጣርታ አልቀርም ብላችሁ ወደ ሀገራችሁ የመጣችሁ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እንኳን ወደ ሀገራችሁ በሰላም መጣችሁ” ብሏል።

“በተለያየ ምክንያት ሀገራችሁ መምጣት ያልቻላችሁ፤ አካላችሁ በያላችሁበት ቦታ ቢሆንም መንፈሳችሁ እዚሁ እኛው ጋር የሆነ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱትን ወገኖቻችሁን http://xn--eyezonethiopia-fb0d.com/ አማካኝነት እያገዛችሁ ስለሆነ ትልቅ አክብሮት አለን” ብሏል።

“ኢትዮጵያ ሰው በሚያስፈልጋት ሰዓት ሰው ሆናችሁ ከአቋማችሁ ሳትዛነፉ፤ ከኢትዮጵያዊነታችሁ ዝቅ ሳትሉ ሀገራችሁን ከፍ ለማድረግ በምታበረክቱት አስተዋጽኦ ኢትዮጵያ አትርፋለችና ምስጋና ይገባችኋል” ብሏል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ።