በጦርነት አካባቢ ሲያስተምሩ ለነበሩ መምህራን የሥነ ልቦናና ማኅበራዊ ድጋፍ ስልጠና እየተሰጠ ነው

መጋቢት 19/2014 (ዋልታ) ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በጦርነቱ አካባቢ ለነበሩ መምህራን የሥነ ልቦናና ማኅበራዊ ድጋፍ ስልጠና  እየሰጠ ይገኛል።

የትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራር የሙያ ፈቃድ ዳይሬክተር ካሳነሽ አለሙ ስልጠናው መምህራን በጦርነት ከደረሰባቸው የሥነ ልቦና ጫና ተላቀው  የመማር ማስተማር ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጣኞችም ከስልጠናው በኋላ በየትምህርት ቤቶቻቸው የተማሪዎችን ሥነ ልቦና ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ካሳነሽ አለሙ

ስልጣኞች ከስልጠናው በኋላ በየዞናቸው ሄደው የአሰልጣኞች ስልጠና እንደሚሰጡም ተገልጿል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ መኳንንት አደመ በበኩላቸው ስልጠናው በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ መገንባት ብቻ ሳይሆን የደረሰውን ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማከም ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ስልጠናውም በክልሉ በሁለት ማእከላት በባሕር ዳርና ደብረ ብርሃን ከተሞች እንደሚሰጥም መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ስልጠና ለ3 ሺሕ 500 መምህራን መሰጠቱም ተገልጿል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!