ሚያዝያ 11/2014 (ዋልታ) በጦርነት የተጎዳ ኢኮኖሚን መልሶ ለማቋቋም የጃፓንን ተሞክሮ የሚያሳይ በአይካ እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተዘጋጀ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ተባባሪ ዲን ጌታነህ መሀሪ (ዶ/ር) ጃፓን ባህልና እሴቷን ጠብቃ የበለፀገች የመጀመሪያዋ አውሮፓዊ ያልሆነች አገር መሆኗን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ታካኮ ኢቶ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት በርካታ የሚያመሳስላቸው ነገሮች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡
ጃፓን የተፈጥሮ ሀብቷንና የሰው ኃይሏን ተጠቅማ እንደበለጸገች ጠቁመው ኢትዮጵያም ይህንን ማድረግ ትችላለች ብለዋል።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጃፓን ምጣኔ ሀብቷን ያሳደገችበት ተሞክሮን በሚመለከት ጽሑፍ እየቀረበ ይገኛል።
በትዕግስት ዘላለም