በጫንጮ ከተማ አሸባሪውን የህወኀት እና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

ነሀሴ 14/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙርያ ዞን አስተዳደር በጫንጮ ከተማ አሸባሪዉን የህወኀት እና ግበረ አበሩን ሸኔ የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
በሰልፉ ላይ ከዞኑ የተዉጣጡ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ነዋሪዎቹ በአባቶቻችን ደም እና አጥንት የተገነባችዉን ሀገር ባንዳዎች እንዲያፈርሱ አንፈቅድም በማለት ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
የኦሮሚያ ልዩ ዞን ፊንፊኔ ዙርያ ዞን አስተዳደሪ ግርማ ሃይሉ በሰልፉ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የሀገራችን ሉዓላዊነት በደም እና አጥንት ዋጋ ተከብረዉ የቆየ በመሆኑ የዛሬ ትዉልድም የአባቶችን አደራ ለመጠበቅ ታሪካዊ ሓላፊነት አለበት ብለዋል፡፡