በ2013 በጀት ዓመት ከውጭ ንግድ 3.62 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

ሐምሌ 16/2013 (ዋልታ) – የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት ከውጭ ንግድ 3 ነጥብ 62 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በ2013 በጀት ዓመት የውጭ ንግድ አፈፃፀሙ 88 በመቶ እንደሆነና ስኬታማ እንደነበር ገልጿል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ በ2013 በጀት ዓመት የተገኘው አፈፃፀም በታሪኩ የመጀመሪያና 88 በመቶ ስኬታማ እንደሆነ አመልክቷል።

የበጀት ዓመቱ ከአምናው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር 19.5 በመቶ ብልጫ መኖሩን ሚኒስቴሩ አክሎ አስታውቋል።

የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ያዛባበት ወቅት እንዲሁም በአገሪቱ ህግ ማስከበር ዘመቻው እንዲሁም ሌሎች በአገሪቱ ላይ የተከሰቱ ክስተቶች በንግዱን እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ መክረሙን የገለፀው ሚኒስቴሩ፣ በተቋማት ደረጃ የተቀናጀ ክትትል በመደረጉ ውጤቱ ሊመጣ ችሏል ብሏል።

(በዙፋን አምባቸው)