በ2022 የሴኡል ማራቶን አትሌት ሞስነት ገረመው የቦታውን ሰዓት በማሻሻል አሸነፈ

ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) በአለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው የ2022 ደቡብ ኮርያ – ሴኡል ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሞስነት ገረመው የቦታውን ሰዓት በማሻሻል አሸነፈ።

አትሌት ሞስነት የቦታውን ሰዓት በማሻሻል (2:04.43) ሲያሸንፍ አትሌት ሄርጳሳ ነጋሳ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።

በተመሳሳይ ዜና የ2022 ካዛኪስታን – ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድርን በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ በቀሉ አበበ ስታሸንፍ በወንዶች ኢትዮጵያዊው ግርማ ጥላሁን 2ኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን ማጠናቀቃቸው ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።