በ2030 ኤች አይቪ/ኤድስ የጤና ስጋት እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ኅዳር 21/2014 (ዋልታ) እ.አ.አ. በ2030 ኤች አይቪ ኤድስ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት እንዳይሆን በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የፌዴራል ኤች አይቪ አዴስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ዓለም ዐቀፍ የኤድስ ቀን በሀገራችን ለ33ኛ ጊዜ በነገው ዕለት “አገልግሎቱን በእኩልነት ለተጠቃሚዎች ማድረስና ወረርሽኙን መግታት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት በኢትዮጵያ 0.86 በመቶ እንደቀነሰ ቢነገርም ተጋላጭ በሆኑና በተለይ በአፍላ ወጣቶች ላይ ያለው ተጋላጭነት ላይ በርካታ ስራዎች መሰራት እንደሚገባው ተነግሯል።

በኢትዮጵያ 60 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ለኤች አይቪ ተጋላጭ መሆናቸውም ተነግሯል።

በዙፋን አምባቸው