በ27 ሚሊዮን 844ሺህ ብር ወጪ የተገነባው የባህል አልባሳት መሸጫ ተመረቀ

 

በሽሮ ሜዳ በባህል አልባሳት ዘርፍ ተሰማርተው ሲሰሩ ለነበሩ የልማት ተነሺዎችና ስራአጥ ወጣቶች የተገነባው የጉለሌ የባህል አልባሳት መሸጫ ማዕከል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

በ27 ሚሊዮን 844ሺህ ብር ወጪ የተገነባውን የመሸጫ ማዕከል ያስመረቁት የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዘመናዊው የባህል አልባሳት መሸጫው የስራ እድል ለተፈጠረላቸው ወጣቶችና ለባህል አልባሳት ዘርፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።

የሽሮ ሜዳው የአልባሳትና እደጥበብ መሸጫ ማዕከል ለ135 ነባር የባህል አልባሳት ነጋዴዎች እና ለ980 ስራ አጥ ወጣቶች ምቹ የስራ ቦታ መሆን ችሏል ተብሏል፡፡
(በደምሰው በነበሩ)