በ3 ወራት የሚሰራ የጋራ መኖሪያ ቤት እና የምገባ ማዕከል ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሦስት ወራት ለሚሰራ የጋራ መኖሪያ ቤት እና የምገባ ማዕከል ግንባታ መሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ።

ከንቲባ አዳነች የክፍለ ከተማውን ነዋሪ የቤት ችግር የሚያቃልሉ እና የ200 አባወራዎችን የቤት ችግር መቅረፍ የሚያስችሉ አራት ህንፃዎች፣ የዳቦ ፋብሪካ እንዲሁም የምገባ ማዕከል ግንባታ ነው ያስጀመሩት።

ከንቲባ አዳነች በመዲናዋ የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግርን ለማቃለል የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው እየተሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የከተማ ግብርናን ማስፋፋት፣ ማዕድ ማጋራት፣ የቤቶች እድሳት እና አቅመ ደካማዎችን ማገዝ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በእመቤት ንጉሴ