በ4 ወራት 157 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን መንግሥት አስታወቀ

ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) የኅልውና ጦርነቱን መሸከም የሚችል ምጣኔሃብት ለመገንባት ባለፉት 4 ወራት ውስጥ 169 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 157 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን መንግሥት አስታወቀ::

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ ይህም ከባለፈው ዓመት አፈጻጸም አንጻር የ24 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡

በወጪ ገበያ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ወደ አሜሪካ የሚላኩ ምርቶች በመሆናቸውና ኢትዮጵያ ከአሜሪካው የቀረጥና ኮታ ነፃ ገበያ እድል (አግዋ) የተሰረዘች በመሆኑ አዳዲስ የገበያ መዳረሻ አማራጮች እየተፈለጉ ነው፡፡

በዚህም ወደ እስያ አገራት በተለይ ደግሞ ቻይናና ህንድ ለመላክ እየተሰራ ነው፡፡

በአፍሪካም ተጨማሪ የገበያ እድሎችን ለመጠቀም ታስቧል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት መንግሥት በአገሪቱ ላይ በምጣኔሃብቱ የሚደርሰውን ጫና ለመመከት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡