በ461 ሚሊዮን ብር የተገነባ ዘመናዊ የአይን ህክምና ማእከል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

መስከረም 2/2015 (ዋልታ) በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል በ461 ሚሊዮን ብር ወጪ ዘመናዊ የአይን ህክምና ማእከል ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ሆስፒታሉ በአይን ህክምና ላይ ሲታይ የነበረውን ረዥም ቀጠሮ የሚያስቀርና እንግልት የሚቀንስ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሪፈር የሚመጡትን በተደራጀ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ማእከሉን የተለየ እንደሚያደርገው ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡