በ5 ወራት ከማዕድን የወጪ ንግድ 241 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) ባለፉት አምስት ወራት ከማዕድን የወጪ ንግድ በተለይም ከወርቅ 241 ሚሊየን ዶላር ገቢ  ማግኘት መቻሉን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ አሁን ካለንበት ሀገራዊ ሁኔታ በተለይም በማዕድን አካባቢዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በመቋቋም የተመዘገው ገቢ አበረታች መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ያሉ ችግሮችን እየፈታንና እየሄድንበት ያለውን መንገድ አጠንክረን ከቀጠልን የማእድን ምርታችን በተለይም  የኢኮኖሚያችን ማገር መሆን እንደሚችል እየታየ ያለው ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል።