በ6.5 ቢሊዮን ብር ለሚገነባ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ግንቦት 19/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጨኪ ቀበሌ በ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው “ጀር ኢንተግሬትድ ፉድ ፋክተሪ” ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የመሠረተ ድንጋዩን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ በተገኙበት ተከናውኗል።
የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ በእውቀቱ ሙሉ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በዚህ አመት መጀመሪያ ሥራ የጀመረ መሆኑን ገልጸው በአሁኑ ወቅት 50 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሷል።
በቀጣይ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ፍጻሜውን ያገኛል የተባለው ፕሮጀክቱ ለ5 ሺሕ ሰዎች የሥራ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ተመጋጋቢነት ያላቸው 11 ፋብሪካዎችን የያዘ ሲሆን ምግብና ምግብ ነክ ነገሮችን ማምረት የሚችል መሆኑ ከዞኑ ብልፅግና ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።