በ70 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ባቲ የእናቶችና ህጻናት ህክምና ሆስፒታል ተመረቀ

ጥር 21/2014 (ዋልታ) በ70 ሚሊዮን ብር ወጪ በአዳማ ከተማ የተገነባው ባቲ የእናቶችና ህጻናት ህክምና ሆስፒታል ዛሬ ተመርቋል።
ሆስፒታሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የማኅበራዊ ጉደዮች አስተባባሪ አብልሃኪም ሙሉ በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡
የሆስፒታሉ ባለቤት ዶክተር አለማየሁ ግርማ ሆስፒታሉ በተለይም የጨቅላ ህጻናትና የእናቶችን ሞት በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መንግሥቱ በቀለ የግል ጤና ተቋማት በፍትሃዊ ክፍያ ኅብረተሰቡን ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በበኩላቸው ስነምግባር የጎደላቸው የግል የጤና ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረው አሁን ጥብቅ ክትትል ይደረግባቸዋል ብለዋል።
ዱጋሳ ፉፋ (ከአዳማ)