በ8 ወራት 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸው ተገለጸ

መጋቢት 10/2013 (ዋልታ) – ባለፉት ስምንት ወራት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በ2013 በጀት ዓመት ስምንት ወራት በተሰራው ጠንካራ የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ሥራ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡

ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ስምንት ወራት አፈጻፀም ጋር ሲነጻፀር  720 ሚሊየን 298 ሺህ 971 ወይንም በ47 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው አመልክተዋል።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ህይወት በመሰዋትና አካልን በመገበር ጭምር ሊያዙ መቻላቸውንም ጠቁመዋል።