በ895 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ ተመረቀ

መጋቢት 5/2014 (ዋልታ) በ895 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህሕት ቤት ህንፃ ተመረቀ።
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የተመረቀው የዋናው ጽሕፈት ቤት ህንፃ በ4 ሺሕ 700 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ መሆኑም ተነግሯል።
ህንፃው ግራውንድና 9 ወለሎችን ያካተተ ሲሆን ምቹ ቢሮዎች፣ የስብሰባ አዳራሾችና ሌሎች አገልግሎቶችን አካቷልም ነው የተባለው፡፡
ህንፃው ብልጽግናን የሚመጥን፣ የፓርቲውን እሴት ያማከለ፣ ወንድማማችነትን የሚያንፀባርቅ እንዲሁም ኅብረ ብሔራዊነትን በሚያጎለብት መንገድ የተገነባ መሆኑም ተመላክቷል።
ህንፃው በአባላት መዋጮና ከደጋፊዎች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በምንይሉህ ደስይበለው