ቢሮ እና ኮሌጁ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት አስጀመረ

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና

ነሐሴ 15/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ጤና ቢሮ እና የነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት አስጀመረ።

በመርኃ ግብሩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አብዱልሃኪም ሙሉ፣ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግሥቱ በቀለ፣ የነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ባለቤት ደ/ር ጉደታ ኢኒካ፣ አባገዳዎች፣ ሀደሲቄዎች እና የአከባቢው ማኅበረሰብ ተገኝተዋል።

ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎቱ በኦሮሚያ ክልል በዚህ በጀት ዓመት ለ500 ሺሕ ሰዎች ሊሰጥ የታቀደ ሲሆን በዚህም በዛሬው ዕለት በነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለ2000 ሰዎች የመስጠት ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።

በዚህ አገልግሎት በቀን ከ300 እስከ 350 ሰዎች የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል።

የህክምናው ዋና አላማ በገንዘብ ዕጦትና በአቅም ማጣት የተነሳ ቤት ውስጥ በጨለማ የሚኖሩትን ወደ ብርሀን ማውጣት ነው ተብሏል።

አሳንቲ ሀሰን (ከአርሲ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!