መጋቢት 1/2013 (ዋልታ)– ባህሬን በትግራይ ክልል ያለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ገለጸች።
በባህሬን የኢፌዲሪ ቆንስላ ጀኔራል ጽህፈት ቤት ቆንስል ጄነራል አምባሳደር ጀማል በክር ከባህሬን ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሻይካ ራና ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የተነጋገሩ ሲሆን ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በክልሉ ያለው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን አመልክተዋል።
በትግራይ ክልል ስላለው የመልሶ ግንባታ ስራዎች ውይይት በተጨማሪ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር አለመግባባት፣ በዜጎች መብትና የበረራ አገልግሎት በሁለቱ እህትማማች አገሮች መካከል ስለሚጀመርበት ሁኔታ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመልክቷል።