ሰኔ 26/ 2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ለአለም አቀፉ የቡና ቅምሻ ውድድር የሚቀርቡ 39 የቡና አይነቶችን ለውድድር አቀረበ::
የቡናን ጥራት ከማረጋገጥ አኳያ ቡና አብቃይ በሆኑ ሀገራት መካከል በሚደረገው የዘንድሮው አለም አቀፍ የቡና ቅምሻ ውድድር የሚቀርቡ በኢትዮዽያ በኩል 30 የቡና አይነቶች ተመርጠው አምስቱ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ ለውድድር የሚላኩ ናቸው ተብሏል::
ኢትዮዽያ የቡና ቅምሻ ውድድር ከገባች ሁለተኛው በሆነው እና የፊታችን ሰኔ 30 በሚካሄደው ውድድር አምስት ቡናዎች ከፍተኛውን ነጥብ በማምጣት ለአለም አቀፍ የቡና ቅምሻ ውድድር ማለፋቸውን የኢትዮጵያቡናና ሻይ ባለ ስልጣን አስታውቋል::
የቡና ቅምሻ ውድድር ጥራት ያለው የቡና አብቃይ የሆኑ ሀገራትን ከውጭ ገበያው ጋር በማስተዋወቅ እንዲሁም ይየቡና አምራቹን ከገበያው ጋር ለማስተዋወቅ እንዲሁም ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እንደሚረዳ የኢትዮጵያቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ተናግረዋል::
(በሄብሮን ዋልታው)