ባለስልጣኑ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች መርሃ ግብር ጀመረ

ሐምሌ 07/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዛሬው ዕለት ችግኝ በመትከል አስጀምሯል፡፡

ባለስልጣኑ  አመራሮችን፣ ሰራተኞችን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ከቁስቋም-እንጦጦ ማሪያም በሚገኘው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት  2 ሺህ ችግኞችን በመትከል ነው መርሃ ግብሩን ያስጀመረው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሞገስ ጥበቡ÷ በተያዘው የክረምት ወራት የ30 ሺህ ችግኞች ተከላን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚከናወኑ መግለጻቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨሪም 15 የሚሆኑ የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ፣ በተመረጡ ሆስፒታሎች እና ትምህርት ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ጥገና ስራዎች እና 50 ለሚሆኑ ችግረኛ ህፃናት ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡