ባለፈው ዓመት የተተከሉ የተዳቀሉ የፍራፍሬ ምርቶች ለቀጣይ ዓመት ለውጪ ገበያ የመድረስ አቅም አሳይተዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ባለፈው ዓመት የተተከሉ የተዳቀሉ የፍራፍሬ ምርቶች ለቀጣይ ዓመት ለውጪ ገበያ የመድረስ አቅም ማሳየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ባለፈው ዓመት የጀመርነው አቮካዶን እና ፓፓያን የማዳቀል ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተከወነ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ዓመት ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን የማድረስ ትልቅ አቅም አሳይቷል” ብለዋል።