ባለፉት 10 ወራት ከ282 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው

ግንቦት 11/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም በሚመለከት ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው እንዳስታወቁት ከሀገር ውስጥ ገቢ እና ከወጪ ንግድ ቀረጥ በተሰበሰበ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር 44 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው።

እንደኢዜአ ዘገባ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 168 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ገቢ ታክስ ሲሆን ቀሪው 113 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተገኘ ገቢ መሆኑን አመልክተዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW