ከ248 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ በ9 ወራት ተሰበሰበ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 267 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 93 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገለጸ፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 248 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን ከሀገር ውስጥ ታክስ ከ145 ነጥብ 2 ቢሊዮን በላይ፤ ከ103 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ መሆኑ ታውቋል።

ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ17 ከመቶ እድገት እንዳለውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡