ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ8 ሺሕ በላይ አዲስ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

ሚያዝያ 30/2014 (ዋልታ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ8 ሺሕ በላይ አዲስ ተማሪዎችን ከሚያዝያ 28/2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተቀበለ መሆኑን አስታውቋል።
የከተማዋ ወጣቶች አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ላሉ ተማሪዎች ከተማሪ ኅብረት፣ ከትራንስፖርትና ስምሪት እና የተማሪዎች ዲን ጽሕፈት ቤት በትብብር በከተማው ከሦስት አውቶብስ ጣቢያዎች እና ከደጃች በላይ ዘለቀ ባሕር ዳር ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል እየተደረገ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው ዘንዘልማ፣ ግሽ አባይ እና ሰላም በተሰኙ ካምፓሶች አቀባበል እያደረገ ሲሆን በሁሉም አውቶቡስ ጣቢያዎች በዩኒቨርሲቲው መኪኖች አቀባበል እየተደረገ ወደ ተመደቡባቸው ግቢዎች የማድረስ እና የተመደቡበትን ዶርሚተሪ የማስረከብ ሥራ እየሰራ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በድረ-ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል።