ባንኩ ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ብር ድጋፍ አደረገ

ነሐሴ 20/2014 (ዋልታ) ወጋገን ባንክ ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ባንኩ በተመሳሳይ ዓምናም ለሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የ500 ሺሕ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ባለፋት 3 ዓመታት ከ70 ሚሊዮን በላይ ወጪ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንና ዘንድሮም 25ኛ ዓመቱን አስመልክቶ የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት ማበርከቱን የባንኩ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ኃይሉ ሞላ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ባንኩ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙን በይፋ ብራንድ አምባሰደሩ አድርጎ መሾሙንም አስታውቋል፡፡

ወጋገን ባንክ ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ.ም 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አክብሯል፡፡

በሳሙኤል ሃጎስ