ባንኩ ለ 650 የመቄዶኒያ ተገልጋዮች የኢፍጣር መርኃ ግብር አዘጋጀ

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲቢኢ ኑር ለ 650 የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ተገልጋዮች ለ 5 ቀናት የሚቆይ የኢፍጣር መርኃ ግብር አስጀመረ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዝዳንት ኑሪ ሀሰን ባንኩ ከመቄዶኒያ በተጨማሪ ከባቡል-ኽይር የበጎ አድራጎት ማኅበር ጋር በመተባበር 1 ሺሕ ሰዎችን ለተከታታይ 5 ቀናት እንደሚያስፈጥር ተናግረዋል።
ባንኩ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች አዲስ አበባን ጨምሮ በዘጠኝ ከተሞች የኢፍጣርና ማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር እያከናወነ መሆኑንም ገልጸዋል።
በኢፍጣር መርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ፣ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶኑሪ ሀሰን፣ የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር መስራችና ሥራ አስኪያጅ ቢኒያም በለጠና ሌሎች የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በትዕግስት ዘላለም
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!