ባንኩ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቀ

መጋቢት 2/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ መረጃቸውን በማስተካከል አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
ባንኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አ.ኤ.አ በ27/08/2021 ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ የደንበኞችን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ሥራ ላለፉት 6 ወራት በመሥራት ላይ መሆኑን አስታውሷል፡፡
እስካሁን በርካታ ደንበኞች መረጃቸውን በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወቅታዊ ማድረጋቻውን አስታውቋል፡፡
ሆኖም እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ያልቻሉ ደንበኞች የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ አግልግሎቶች ብቻ ማለትም (የሞባይል ባንኪንግ፣ የኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲሁም የኤቲኤም እና የፖስ አገልግሎት) እንደሚቋረጥባቸው ገልጿል።
ይሁን እንጂ ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ ግን ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች በመምጣት መረጃቸውን ሲያስተካክሉ ወዲያውኑ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡