ብሄራዊ ምክክሩ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርገውን እውነት ጨምቆ ለማውጣት የሚረዳ ነው – መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)

የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

ግንቦት 21/2016 (አዲስ ዋልታ) ብሄራዊ ምክክሩ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርገውን እውነት በምክክር ሂደቱ ጨምቆ ለማውጣት የሚረዳ ታሪካዊ ሀገራዊ ምክክር መሆኑን የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ላይ ምክክሩ በስርዓት ሲከወን የሚያመጣውን መልካም ጎን ለጎረቤት የአፍሪካ ሀገራት ጭምር ማስተማሪያ እንዲሆን በሚችልበት መልኩ ይሰራል ብለዋል፡፡



በልዩነታቸው አንድ የሆኑ ሕዝቦች የሚኖሩባት ሀገሪቱ ከሰላም ወደ ጦርነት፣ ከፍቅር ወደ ጥላቻ የሚወስዷትን ምክንያቶች በምክክር አንጥሮ በማውጣት ወደ መግባባት መድረስ እና ሀገሪቱን ወደ እድገት ጎዳና መምራት ብቸኛ አማራጭ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

መተማመን የሰፈነበት አዲስ የፖለቲካ ስርዓት ለመፍጠር፣ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን ችግር መፍትሄ ለመስጠት እና ወቅታዊ ችግራችንን ዘላቂ በሆነ መልኩ በመፍተታ እንዲሁም ሰላሟ የተረጋገጠች እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ያላት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የምክክሩ አላማ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ