ብልፅግና ኢትዮጵያን ከፈተናዎቿ የሚያሻግር ብቁ አመራር መፍጠር አንዱ አቅጣጫዬ ነው አለ

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያን ከፈተናዎቿ ሊያሻግር የሚችል ብቁ አመራር መፍጠር የብልፅግና ፓርቲ አንዱ አቅጣጫ መሆኑን የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ።

በሀረሪ ክልል ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ አገራዊ እመርታ ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ግቦችን በማሳካት ተጠናቋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ እንደገለጹት ኢትዮጵያን ከፈተናዎቿ ሊያሻግር የሚችል ብቁ አመራር መፍጠር የብልጽግና ፓርቲ አንዱ አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል።

አመራሩ አሁን እየገጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችን በጽናት በመታገል ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በመጀመሪያ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ የተቀመጡ የሥራ አቅጣጫዎችን በዕቅድ በመያዝ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከኅብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በተጠናከረ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባም ገልጸዋል።

አመራሩ አቅሙን በማጎልበት ወቅቱን የሚመጥን አመራር መስጠት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የክልሉን ሕዝብ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ የአመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አያይዘውም ተመሳሳይ የስልጠና መድረኮች እስከታችኛው የአመራር እርከን ተጠናከሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያሳያል፡፡