ብልፅግና ፓርቲ በሐረሪ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ

መጋቢት 24/2013 (ዋልታ) – ብልፅግና ፓርቲ በሐረሪ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ በይፋ ማካሄድ ጀምሯል።

የፓርቲው አባላት በሐረር ከተማ በተለምዶ “ሐማሬሳ” አካባቢ ላይ በመዘዋወር የድጋፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ከትናንት ጀምሮ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

በቅስቀሳው ወቅትም ፓርቲው የልማት፣ የአንድነት እና የብልጽግና መሆኑን አመላክተዋል።

በቅሰቀሳው የብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሐመድ ጨምሮ ሌሎችም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣አባላት እና ደጋፊዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።