ሰኔ 08/2013 (ዋልታ) – የብልፅግና ፓርቲ በምዕራብ ሸዋ ዞን በአምቦ ከተማ የምረጡኝ ዘመቻ አካሂዷል።
የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ዲሪርሳ ዋቁማ 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ እና የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌትን በሰላምና በስኬት ለማጠናቀቅ ብልፅግና ይሰራል ብለዋል፡፡
በምረጡኝ ዘመቻ መርኃግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ፍቃዱ ተሰማ ለውጡ የሀገር ሁለንተናዊ መሠረት መሆኑን ገልጸው፣ በዚህም በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አመርቂ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
ፖርቲያችን በእውቀት እና ቴክኖሎጂ የተፈጥሮ ሀብቶችን ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ልማትና የስራ እድሎችን መፍጠር እንዲሁም የህዝቡን ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን በመመለስ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
የምርጫ ካርዱን የወሰደ ሁሉም ዜጋ ዴሞክራሲያዊ መብቱን እንዲጠቀምበትም መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በምረጡኝ ዘመቻው ላይ የተለያዩ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
(በሚልኪያስ አዱኛ)