ብሮድካስት ባለስልጣን በግጭት አዘጋገብ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የስልጠና እና የምክክር መድረክ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በግጭት አዘጋገብ ሁኔታ ላይ የሚያተኩር የስልጠና እና የምክክር መድረክ ለሚመለከታቸው የሚዲያ አካላት አዘጋጅቷል።
ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ መድረክ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የሚዲያውን አቅም ለመገንባት ብሎም በሀገራችን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ለማስገባት የዚህ መድረክ መዘጋጀት ተገቢ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዩን ተክሉ አገራዊ ገፅታን ለመገንባት የማህበራዊ ሚዲያ ድርሻ ከፍ ያለ በመሆኑ ትኩረት ሰጥተን በትክክለኛ እና አመዛዛኝ መልኩ ልንገነባው ይገባል ብለዋል።
በዚህ የምክክር እና የስልጠና መድረክ በቀውስ ወቅት የሚዲያ ሚና፣ የዲጂታል ማህበራዊ ሚዲያ አዘጋገብ፣ እንዲሁም ስርአተ ፆታን መሰረት ያደረገ አዘጋገብን በተመለከተ ውይይቶች ይደረጉበታል ተብሏል።
(በቁምነገር አህመድ)