ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን የቤተክርስትያኗ መገናኛ ብዙኃን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

ቅዱስነታቸው ሰሞኑን ባደረባቸው ህመም የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸው መቆየቱ ይታወሳል።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በ1980 ዓ.ም ነሐሴ 29 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ተብለው የተሾሙ ሲሆን ላለፉት 34 አመታት በፓትርያርክነት አገልግለዋል።

ብጹዕ ወቅ አቡነ መርቆሬዎስ የቤተክርስቲያኗ ትምህርት የሆኑትን አቋቋም፣ ድጓና ዝማሬ መዋስዕት በላቀ ሁኔታ የተማሩ መሆናቸውን ከሕይወት ታሪካቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።