ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በቦረና ዞን በድርቅ ምክንያት የተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጎበኙ

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ፣ አምባሳደሮች እና የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቦረና ዞን በድርቅ ምክንያት የተጎዱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጎብኝተዋል።

ልዑኩ ቦረና ሲደርስ አባ ገዳዎች አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን በአካባቢው የደረሰውን ጉዳት በመምልከት ድጋፍ ለሚያስፈልገው የኅብረተሰብ ክፍል ድጋፍ አድርጓል፤ ከኅብረተሰቡ ጋርም ውይይት አድርጓል።

የዘንድሮው ድርቅ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው ዝናቡ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ እንደሆነ እና በዚህም ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን የአካባቢው አርብቶ አደሮች ተናግረዋል።

አባ ገዳዎች በበኩላቸው በተለያዩ አካላት ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም ከደረሰው ጉዳት ጋር ሲነፃፀር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ገልጸው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ኢብኮ ኦቢኤንን ጠቅሶ ዘግቧል።

አካባቢውን እየጎበኘ ያለው ልዑክ በዱቡሉቅ ወረዳ በመገኘት ANE በተባለ በጎ አድራጊ ድርጅት የተዘጋጀውን 600 ኩንታል የምግብ እህል፣ 20 ሺሕ ኪሎ ግራም የተመጣጠነ ምግብ እና 6 ሺሕ ሊትር ዘይት ለ1 ሺሕ 200 አባዎራዎች አስረክቧል።