ቱርክ መንግሥት ለሰብኣዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑ ትክክለኛ እርምጃ ነው አለች

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) ቱርክ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብኣዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑ ትክክለኛ እርምጃ ነው ስትል ገለጸች፡፡

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ በወጣው መልዕክት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብኣዊነት ግጭት ለማቆም ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ እንደምትቀበል አስታውቃለች።

መንግሥት ለሰብኣዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑ ለግጭቱ መፍትሄ ለማፈላለግ ትክክለኛ እርምጃ ነውም ብሏል በመግለጫው።

ቱርክ ውሳኔው ዘላቂ ሰላም እንደሚያስገኝ ያላትን እምነት የገለጸች ሲሆን የሰብኣዊ እርዳታ ለትግራይ ክልል እንዲሁም ለሌሎች ክልሎች እንደሚዳረስ ተስፋ እናደርጋለን ብላለች፡፡