የጎዳና ላይ ኢፍጣር በመጪው ዓርብ አዲስ አበባ ይካሄዳል

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) በመጪው ዓርብ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርኃ ግብር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የ”ከዒድ እስከ ዒድ” አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።

መርኃ ግብሩን ለመታደም እንግዶች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ሀገራቸው በመግባት ላይ እንደሚገኙ የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ገልጸዋል።

ከዒድ እስከ ዒድ ጥሪን ለማስተባበር እስካሁን ከ2 ሺሕ 500 በላይ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል ያሉት ኡስታዝ አቡበከር በመጪው ረቡዕ የዒድ ኤክስፖ መርኃ ግብር እንደሚከፈትም ተናግረዋል።

መርኃ ግብሩ የኢትዮጵያን በጎ ጎን ለዓለም ማስተዋወቂያ ዕድል እንደሚፈጥርም መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀደም ሲል ዒድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የዒድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW