ቴሌብር ለግብር ከፋዮች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናገሩ

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) የቴሌብር አከፋፈል ግብር ለመክፈል የሚወስደውን ግዜ በመቆጠብ እና ግልጽ በመሆኑ ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ነው ሲሉ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናገሩ፡፡

የቴሌብር አከፋፈል ትግብራን በተመለከተ የመስክ ጉብኝት እየተደረገ ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ የተቋሙ ሠራተኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የመስክ ምልከታው የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮችና በመንግሥት ድጎማ የተደረገበት የነዳጅ ግብይት ነው።

ክፍያዎች በቴሌብር መደረጉ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲኖር ከማስቻሉም በላይ ተአማኒ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ዲጂታል ሲስተምን በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዲጂታል አሰረሰር ሲጀመር ተግዳሮቶች አይጠፋም ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ ይሁን እንጂ በአመራሮችና በመላው ሕዝብ ጥረት ማሳካት ይቻላል ብለዋል።

በተለይ ሀገርን ለማልማት ግብርን የሚከፍል ሰው መንገላታት ስለሌለበት ባለበት ሆኖ ክፍያ መፈጸም ማስቻል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቴሌብር አከፋፈል ግብር ለመክፈል የሚወስደውን ግዜ በመቆጠብ እና ግልጽ በመሆኑ ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባትና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።

በመስከረም ቸርነት