ትሕነግ በሰሜን ሸዋ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት መዝረፉን ጥናት አረጋገጠ

ታኅሣሥ 24/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግ በሰሜን ሸዋ በወረራ ይዞቸው በነበሩ አካባቢዎች 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የግለሰቦች ቤት ዝርፊያና ውድመት ማድረሱ ተገለጸ፡፡

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ጥናት የሽብር ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች የሚገለገሉባቸውን የቤት ቁሳቁስ መዝረፉን አረጋግጧል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የጥራትና ምርምር ተባባሪ ዲን አራጋው አለማየሁ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደተናገሩት ቡድኑ በተለያዩ የሕዝብ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት መፈጸሙን አስታውሰው ቡድኑ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ዝርፊያና ውድመት ያስከተለው በግለሰቦች የቤት ቁሳቁስ ላይ ብቻ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም የአማራን ሕዝብ የከፋ ድህነት ውስጥ ለመክተት አስቦና አልሞ ያደረገው መሆኑን ገልጸዋል።
በሰሜን ሸዋ በትምህርት ተቋማት ላይም አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በአጣዬ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ላይ ብቻ ከ54 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል።