ትምህርታቸውን በጎንደር ሲከታተሉ የቆዩ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተመረቁ

ሚያዚያ 8/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በከፈተው ጦርነት ምክንያት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ 85 የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተማሪዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ ተመርቀዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንት ተወካይ ካሳሁን ተገኘ (ዶ/ር) ለተመራቂ ተማሪዎቹ በሰጡት የሥራ መመሪያ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ 740 ተማሪዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን መቀጠላቸውን ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን አጠናቀው በመመረቃቸው መደሰታቸውን እና ያሳለፉት ችግርም በቀጣይ ለፈተናዎች ዝግጁ እንዲሆኑ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል።

የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማኅበረሰብ ልጆቻቸው እስኪመረቁ ላደረገው አስተዋጽኦ ያላቸው አክብሮት ላቅ ያለ መኾኑን መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።