ቻይና ኢትዮጵያ ያደረገችውን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደምትደግፍ አስታወቀች

ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) – ቻይና የኢትዮጵያን የተናጥል ተኩስ አቁም ጥሪ እንደምትደግፍ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን አማካኝነት አስታወቃለች፡፡

ቃል አቀባዩ “እኛ አትዮጰያዊያን የውስጥ ችግራቸውን በራሳቸው አቅም የመፍታት ጥበብ እንዳላቸው እናምናለን” ብለዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ እየቀረበ ባለው የዝናብ ወቅት በክልሉ የሰብዓዊ ዕርዳታን እንዲሁም የግብርና ሥራዎችን ለማመቻቸት ያለመ መሆኑን ዘ አፍሪካን ሪፖርት እና ሲ ጂ ቲ ኤንን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀረበውን የተኩስ አቁም ጥያቄን ተከትሎ ግጭት በተቀሰቀሰበት ትግራይ ክልል የኢትዮጵያ መንግስት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ማድረጉ ይታወሳል፡፡