ቼክ ሪፐብሊክና ኢትዮጵያ ከ400 ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጣ የኮቪድ-19 መከላከያ የድጋፍ ስምምነት አደረጉ

መጋቢት 17 ቀን 2013 (ዋልታ) – የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ፓቬል ሚክስ ከ440 ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጡ የኮቪድ-19 መከላከያ የህክምና ቁሳቁሶች የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

“የኢትዮጵያን የኮቪድ-19 መከላከል አቅም ማጠናከር” የተሰኘ የድጋፍ ስምምነት በቼክ ሪፐብሊክና በኢትዮጵያ መካከል መደረጉን በኢትዮጵያ ከቼክ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።