ናይጀሪያዊቷ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ የአለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ሆኑ

አዲሷ የአለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ

የካቲት 09፣ 2013 (ዋልታ) – ናይጀሪያዊቷ ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ የመጀመሪያዋ ሴትና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊ የአለም ንግድ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ተሹመዋል።

የአዲሷ ናይጀሪያዊት ሹመት የፀደቀው የድርጅቱ አጠቃላይ ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ አድርጎ ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ነው።

የአለም ንግድ ድርጅት በአሁን ወቅት በአገራት መካከል ያለውን የንግድ ግጭት፣ ሀገራት እርስ በርሳቸው ታሪፍ መጣላቸው እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለው የኢኮኖሚ ችግር መፍትሄ ሊሰጣቸው የሚገቡ መሆናቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

የቀድሞ የናይጀሪያ የገንዘብ ሚኒስቴር ዶክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢውያላ የአለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርም ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የክትባት ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለመው ዓለም አቀፍ የክትባት ጥምረትን ይመሩ ነበር።