አማራ ክልል ሰርጎ የገባው የአሸባሪው ህወሀት ታጣቂ ከአማራ ሚሊሻና ልዩ ሀይል አቅም በታች ነው

May be an image of 1 person and military uniform
ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) –
አማራ ክልል ሰርጎ የገባው የአሸባሪው ህወሀት ታጣቂ ከአማራ ሚሊሻና ልዩ ሀይል አቅም በታች መሆኑን የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
አሸባሪው ህወሓት እስካልጠፋ ድረስ “ወደፊትም የሀሰት ወሬና ማወናበድ አይጠፋም:: ህዝቡም ከዚህ ውዥምብር መውጣት አለበትም ተብሏል።
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ተሰጥተዋል።
አሸባሪው ህወሓት በራያ በኩል በጉባ ላፍቶና ሀብር ወረዳዎች በአካባቢው ህዝብ የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲሳነው ትጥቁን እየጣለ መፈርጠጡን ገልጸዋል።
የአማራ ሚሊሻ የማረካቸውን የህወሓት ሰርጎ ገቦች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረከበ መሆኑን ጠቆመው፤ የማረኩትን የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ራሳቸው እንዲያጠናክሩበት መደረጉን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ የደረሰበትን ኪሳራ መቋቋም አቅቶት የፈረጠጠው የአሸባሪው ሀይል ወደ ጋሸና፣ ተኩለሽና ቁልመስክ በመሸሽ በለመደው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን እያወናበደ መሆኑን ገልጸዋል።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን እስካልጠፋ ድረስ የሀሰት ወሬና ማወናበድ ስለማይጠፋ ህብረተሰቡ ህጋዊ ከሆነ የመንግሰት አካል የሚሰጠውን መረጃ ብቻ በመከተል ከውዥንብሩ መውጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በተከዜ በኩል በከፈተው ጥቃት ከፍተኛ ኪሳራ ስለደረሰበት ካሁን በፊት እንዳደረገው አስከሬን በሲኖ ትራክ ጭኖ መሄድ አልቻለም ብለዋል።
ከዚህም ባለፈ ምንም ዓይነት የውጊያ ስልት የማያውቁ ንጹሃንን በግድ ወደ ትግል በማስገባት ተከዜ ላይ የውሃ ሲሳይ ሆነው እንዲቀሩ ማድረጉን ጠቁመው፤ በውጊያ የሞቱትን መቅበር ስላልቻለ አስክሬናቸውን ተከዜ ወንዝ ላይ እንደጨመረ ተናግረዋል።
ይህ እኩይ ድርጊቱ አልበቃው ብሎ በለመደው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በተሳሳተ መረጃ “አለም አቀፉን ማህበረሰብ ጭምር ማወናበድ ጀምሯል” ብለዋል።