አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያቀረበችውን ጥያቄ ቻይና እና ሩሲያ አገዱት

ጥር 13/2014 (ዋልታ) አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ለተባበሩት መንግሥታት ያቀረበችው ጥያቄ በቻይና እና ሩሲያ መታገዱ ተሰማ፡፡
ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ማስወንጭፏን ተከትሎ በ5 ሰሜን ኮሪያዊያን ላይ ማዕቀብ እንዲጣል አሜሪካ ያቀረበችው ጥያቄ ነው በቻይና እና በሩሲያ የታገደው፡፡
ቻይና የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ላይ ዝግ ስብሰባ ከማድረጉ በፊት በአገሪቱ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ከዋሽንግተን የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ ያደረገች ሲሆን ሩሲያም በተመሳሳይ መንገድ የአሜሪካን የማዕቀብ ጥያቄ መቃወሟ ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አባል አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የሁለቱን አገራት ውሳኔ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ቻይና እና ሩሲያ ጥያቄያችንን ውድቅ ማድረጋቸው በአሜሪካ ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም ስለማለታቸው የውጭ አገራት መገናኛ ብዙኃን እየተቀባበሉት ነው።