አሜሪካ በትግራይ ለተፈናቀሉ ዜጎች 1,500 ጊዜያዊ መጠለያ ድጋፍ አደረገች

ሚያዚያ 08/2013 (ዋልታ) – የአሜሪካ መንግስት በትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ጊዜያዊ መጠለያ ለመስራት የሚያስችሉ 1ሺህ 500 ጥቅል ፕላስቲክ ሼልተሮች ድጋፍ አደረገች።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ እንደገለፁት ሼልተሩ በትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ በ10 ሺህዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ጊዜያዊ መጠለያነት እንደሚያገለግል አብራርተዋል።
የአይ ኦ ኤም ሚሽን ዳይሬክተር በበኩላቸው ድጋፉ መድረስ ላለበት ዜጎች የማድረሱን ስራ ከዛሬ እንጀምራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ባለፉት 5 ወራት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር 500 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ የሰብአዊ ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት አምባሳደሯ በቀጣይም በመላው ሀገሪቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል።
(በትዕግስት ዘላለም)