የካቲት 16/2014 (ዋልታ) የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ፆታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶችን መፈጸማቸው መገለጹ በእጅጉ እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸች።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጉዳዩን በተመለከተ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት የሕወሓት ታጣቂዎች በ2013 ዓ.ም ነሐሴ ወር መጨረሻ እና በ2014 ዓ.ም መስከረም መጀመሪያ አካባቢ በአማራ ክልል አሰቃቂ ድርጊቶችን እንደፈፀሙ መግለጹን አስታውሷል።
ሁሉም ወገኖች በሰብኣዊነት ላይ የሚፈፀም ጥቃት እና በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው በደል እንዲቆም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ጥሪ አቅርበዋል።
ቃል አቀባዩ ግጭቱን ለማስቆም እና ለሁሉም ተበዳዮች ፍትሕን ለማረጋገጥ ጊዜው አሁን ነው መለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።